የቃና ሳተላይት እና ፍሪክዌንሲ
ናይልሳት 102 (7 ዲግሪ W)
ሞገድ: 12226
ድረ ገጽvs ድህረ ገጽ: ሆሪዞንታል
ሲምቦል ሬት: 27.500
FEC: 3/4

ሰኔ 13/2010
 

የራስ ምርኮኛ

አርቱሮ ሞንቴኔግሮ እና ኤላዲዮ ጎሜዝ ሉና በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ በባላንጣነት የሚፈላለጉ የስራና የሕይወት ተፎካካሪዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ከገንዘብ ሽሚያ በላይ የሚፋለሙባት ዋና ምክንያት ኤላዲዮን ከማግባቷ በፊት ከአርቱሮ ጋር የፍቅር ጊዜ ያሳለፈች ጁሊያ የተባለች ሴት ናት፡፡ ጁሊያና አርቱሮ ጥልቅ ፍቅር የነበራቸው ቢሆንም አርቱሮ ሌላ ሴት ማስረገዙን ስታውቅ ዳግም ላታገኘው ተሰናበተችው፡፡ ለሀያ አመታት ከኤላዲዮ ጋር ያሳለፈችው ጁሊያ ወንድ ልጅ ወልዳለታለች፡፡ መሀንዲሱ ልጇ ዴቪድ ዳግም በሕይወቴ አላይህም ካለችው ከአርቱሮ ልጅ ጋር ፍቅር ይጀምራል ብላ ግን አስባ አታውቅም፡፡ ዴቪድ ሬጂና ከተባለችው የአርቱሮ ሞንቴኔግሮ ልጅ ጋር ፍቅር ከመጀመሩ በፊት ደግሞ ዳኒየላ ከተባለችው ሌላ ልጁ ጋር ለጥቂት ቀናት የቆየ ግንኙነት ነበረው፡፡ በሌላ በኩል፤ ታዋቂው ባለሃብት ኤላዲዮ በትዳሩ ላይ ሲማግጥ፤ ራሱን ኤሪክ ከተባለው የአርቱሮ ልጅ ጋር አንድ ሴት ተጋርቶ ያገኘዋል፡፡ታሪኩ እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፍቅር እና የቤተሰብ ግንኙነቶችን እያሳየ፤ በእያንዳንዷ የቤተሰብ ሚስጥር መገለጥ ተመልካችን እያስገረመ ይቀጥላል፡፡​

Program Info

ክፍል: 
ተከታታይ
ቀን: 
ጨርሷል
Yes