የቃና ሳተላይት እና ፍሪክዌንሲ
ናይልሳት 102 (7 ዲግሪ W)
ሞገድ: 12226
ድረ ገጽvs ድህረ ገጽ: ሆሪዞንታል
ሲምቦል ሬት: 27.500
FEC: 3/4

ኅዳር 15/2010
 

ቅጣት

ቅጣት ፋትማጉል እና ከሪም በሚባሉ ዋና ገፀ ባሕሪት ዙሪያ የሚያጠነጥን በውጣ ውረድ የተሞላ ታሪክ ነው፡፡ የትንሽ መንደር ነዋሪ የሆነችው ፋትማጉል አንድ ምሽት በሶስት በአልክሆል እና እፅ የተገፋፉ ወንዶች ትደፈራለች፡፡ የደፋሪዎቹ ኤርዶሀን ፣ ሳሊም እና ቩርል ጓደኛ የሆነው ከሪም በድርጊቱ ባይሳተፍም በቦታው ኖሮ እነሱን ባለማስቆሙ ይፀፀታል፡፡ ጠበቃ የሆነው የሁለቱ ደፋሪዎች አጎት እና የሶስቱም ሀብታም ወላጆች የፋትማጉል ቤተሰብን በገንዘብ በመደለል ፋትማጉል ከሪምን ያለፍላጎትዋ እንድታገባው ያደርጋሉ፡፡ ይህ ዜና የፋትማጉል እጮኛ የነበረውን ሙስጠፋ  በፋትማጉል እና ከሪም ላይ ለበቀል እንዲነሳሳ በማድረጉ ሁለቱም መንደራቸውን ለቀው ወደ ኢስታንቡል ይሄዳሉ፡፡ ቅጣት ከሪም በሂደት ከፋትማጉል ጋር ፍቅር ሲይዝው እና ደፋሪዎቹዋን ለማጋለጥ በምታደርገው ጥረት ከጎንዋ ሲሆን ያሳያል፡፡ 

 

Program Info

ክፍል: 
ተከታታይ
ቀን: 
ከስኞ እስከ አርብ
ጊዜ: 
ማታ 2፡00 ሰአት ላይ
Yes