የቃና ሳተላይት እና ፍሪክዌንሲ
ናይልሳት 102 (7 ዲግሪ W)
ሞገድ: 12226
ድረ ገጽvs ድህረ ገጽ: ሆሪዞንታል
ሲምቦል ሬት: 27.500
FEC: 3/4

ሰኔ 13/2010
 

ቃና ፓስፖርት

13.10.2010

የዱር ግንኙነቶች - ይህ ተከታታይ ዝግጅት በአለማችን አህጉራትን መካከል ያሉትን አስደናቂ ተመሳሳይነት እና ልዩነቶችን ያሳየናል እናም በነዚህ ሁለት ቦታዎች መገናኛ ድልድዮች ላይ የሚገኙ የተለያዩ እንስሳቶች ሲገናኘኙ እናያለን፡፡ እነዚህ በሁለት አህጉራት መካከል ያሉት የተፈጠሮ ድልድዮች በአሀጉራቱ ያሉትን ዕፅዋት እና እንስሳት ለመገናኘት የሚያስችላቸው ለየት ያሉ ቦታዎችን ይፈጥራሉ፡፡ ሰሜን እና ደቡብ አሜሪካን የሚያገናኝ ጠባብ መሬት ከሁለቱም አህጉራት የመጡ ዝርያዎችን በደንብ ያሳዩናል፡፡ ሁሉም ዝርያዎች ከሰሜን እና ከደቡባ አሜሪካ መጥተው አዲስ ቤት ሰርተዋል፡ ከሁለቱም ጋር ሲነፃፀር አዲስ መሬት የሆነው፡ መካከለኛ አሜሪካ፡፡
ከፍተኛ የስሜት ህዋሶች - አንዳንድ እንስሳት በጣም የተለየ የስሜት አካላት ለምን እንዳላቸው አስባችሁ ታውቃላችሁ? እባቦች ለምንድን ነው መንታ ምላስ ያላቸው? ዝሆኖች ለምንድን ነው ትልቅ ጆሮ ያላቸው? አንዳንድ የሌሊት ወፎች ለምንድን ነው የተለዩ አፍንጫና ጆሮ ያላቸው? እሳት ራቶች ለምንድን ነው አንቴናቸው ላባ ያለው የሚመስለው? ሁሉም አካላት የእንስሳውን ደህንነት ለመጠበቅ እንዲያስችለው የሚሰጠው ዓላማ አለው፡፡ ልክ እንደ እኛ፣ እንስሰትም እርስ በርሳቸው ለመነጋገር፣ የሚሄዱበትን አቅጣጫ ለማወቅ፣ ምግብ ለማግኘት እናም ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ስሜቶቻቸውን ይጠቀማሉ፡፡